Ethiopia

[email protected]
HOME NEWS PRESS CULTURE EDITORIAL ARCHIVES CONTACT US
HOME
NEWS
PRESS
CULTURE
RELIGION
ARCHIVES
MISSION
CONTACT US

LINKS
TISJD Solidarity
Abbay Media
Ethiopian News
Dagmawi
Justice in Ethiopia
Ethio Quest
MBendi
AfricaNet.com
Index on Africa
World Africa Net
Africalog

 

INT'L NEWS SITES
Africa Confidential
African Intelligence
BBC
BBC Africa
CNN
Reuters
Guardian
The Economist
The Independent
The Times
IRIN
Addis Tribune
All Africa
Walta
Focus on Africa
UNHCR

 

OPPOSITION RADIO
Radio Solidarity
German Radio
Voice of America
Nesanet
Radio UNMEE
ETV
Negat
Finote Radio
Medhin
Voice of Ethiopia

 

DEJE SELAM ደጀ ሰላም

ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን - ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ

Thursday, July 9, 2009


/ሲኖዶስ የፓትርያርኩንሁሉን አቀፍ ሥልጣንገፈፈ፣እንደራሴሾመ


(
ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 8 እና 9/2009)
ትናንት ማታ የተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ታሪካዊ ስብሰባ በእምቢተኝነታቸው የጸኑትን ፓትርያርክ ሥልጣን በመግፈፍ እንደራሴ ሾመባቸው። ትናንት የስብሰባው ቃለ ጉባዔ በተነበበበት ጊዜ እንደተገለጸው ቅዱስነታቸው ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች በሙሉ ተገልለው፣ በጸሎት ብቻ ተወስነው እንዲኖሩ፣ ለዚህም አስፈላጊው ነገር ሁሉ እንዲሟላላቸው፣ በእንደራሴነት ደግሞ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ እንዲሰየሙ ወስኗል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰሞኑን ባደረገው ሙከራ ቅዱስነታቸው ነገሮችን በጥሙና እንዲመለከቱና በሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲመሩ አባቶች በእንባ ጭምር የለመኗቸው ቢሆንም ቅዱስ ፓትርያርኩ ግን ማንንም ለመስማት ሳይችሉ ቀርተዋል። በርግጥም ቃለ ጉባዔው በሚፈረምበት ቀን ማለትም ሐሙስ ጁላይ 9 ጠዋት ውሳኔው ቀድሞ እንደተነበበው ሆኖ ካለፈ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ ሥራው በእንደራሴው ይመራል ማለት ነው። ይህ ማለት ግን እንደ ቀድሞ ፓትርያርክ ከሥልጣናቸው ወርደዋል ማለት እንዳልሆነ አንድ አባት ለደጀ ሰላም አብራርተዋል። ምናልባት ግን ቅዱስነታቸው በተለመደው ጠባያቸው (የነ / እጅጋየሁን ምክር ተከትለው) ከሄዱ የአቡነ መርቆርዮስ ዓይነት መጨረሻ ይገጥማቸው ይሆናል ተብሎ ተሰግቷል።
 
ከእንደራሴው ሹመት በተጨማሪ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ሹም ሽር የሚደረግ ሲሆን በተዋረድም በቅዱስነታቸው ቤተ ሰቦች ተይዘው የነበሩ ታላላቅ የአገልግሎት መምሪያዎች ሃላፊነቶች በሙሉ ለቦታው በሚመጥኑ ሊቃውንት ይሰጣሉ ተብሏል። ይህንኑ አጠቃላይ ሒደት የተመለከቱ አንድ አባትእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሥራውን እየሠራ ነውብለዋል።
እንደራሴነት ምን ማለት ነው የሚለው ጉዳይ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተመሳክሮ ማብራሪያ መሰጠት እንዳለበት እያመንን ለጊዜው ግን ከዚህ ቀደም የነበረ አንድ ታሪክ ለማስታወስ እንወዳለን። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ (የመጀመሪያው ፓትርያርክ) በዕድሜና ጤና ምክንያት ሥራቸውን መሥራት ባልቻሉባቸው የመጨረሻ ዓመታት ሁዋላ 2 ፓትርያርክ የሆኑት ሰማዕቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስእንደራሴሆነው ቤተ ክርስቲያንን ሲመሩ ቆይተዋል። መንበሩ ግን የፓትርያርኩ እንደሆነ ዘልቋል። በቅዳሴ ወቅት የሚነሣውም የእንደራሴው ስም ሳይሆን የፓትርያርኩ ስም ነበር።
መጨረሻውን ያሳምረው!!!!!