በውጭ
ጉዳይ
ሚኒስቴር
አሳሳቢነት
ጥሩነሽ
ዲባባ
እና
ጌጤ
ዋሚ
መሬት
እንዲመልሱ
ታዘዙ
በአሰግድ
ተፈራ
ከሳዑዲ
አረቢያ
ኤምባሲ
ተወስዶ
ለአትሌት
ጌጤ
ዋሚና
ለአትሌት
ጥሩነሽ
ዲባባ
የተሰጠውን
መሬት
የውጪ
ጉዳይ
ሚኒስቴር
ተመልሶ
ለኤምባሲው
እንዲሰጥ
የሰጠው
ትዕዛዝ
ተፈፃሚ
እንዲሆን
የአዲስ
አበባ
አስተዳደር
ሥራ
አስኪያጅ
አሳሰቡ፡፡
ሥራ
አስኪያጁ የውጪ
ጉዳይ ሚኒስቴር
የፃፈውን ደብዳቤ
በመጥቀስ ለመሬትና
ይዞታ አስተዳደር
የፃፉት ደብዳቤ
እንደሚያስረዳው ሁለቱ
አትሌቶች ከአራት
ዓመት በፊት
የሊዝ ኪራይ
ዋጋ ከፍለው
የወሰዱት መሬት
ለሳዑዲ ኤምባሲ
እንዲመለስ የተሰጠው
የጊዜ ገደብ
ሁለት ሳምንት
ብቻ ነው፡፡
ቀደም ሲል
የሳዑዲ ኤምባሲ
ቦሌ ዓለም
ሕንፃ ፊት
ለፊት ይዞት
የነበረውን ቦታ
ለኤምባሲው ደህንነት
አመቺ ባለመሆኑ
አስተዳደሩ መሬቱን
ለሌላ ወገን
ቢሰጠው እንደሚስማማ
ገልፆ ደብዳቤ
ፅፎ ነበር፡፡
ከአስተዳደሩ የተገኘው
መረጃ እንደሚያመለክተው
መሬቱ በድጋሚ
ለኤምባሲው እንዲሰጥ
የውጪ ጉዳይ
ሚኒስቴር በደብዳቤ
ጥያቄ ያቀረበው
ኤምባሲው በድጋሚ
መሬቱ ይመለስልኝ
ብሎ በመጠየቁ
ነው፡፡
የኤምባሲውን ጥያቄ
ጠቅሶ ውጪ
ጉዳይ ሚኒስቴር
ለአዲስ አበባ
አስተዳደር በፃፈው
ደብዳቤ "በሳዑዲና
በኢትዮጵያ መካከል
የቆየው ግንኙነትና
ትስስር ይበልጥ
እንዲጠናከር" ሲባል
መሬቱ እንደገና
ለኤምባሲው እንዲመለስ
ይጠይቃል፡፡
የአዲስ አበባ
አስተዳደር ሥራ
አስኪያጅ መሬቱ
ለኤምባሲው እንዲመለስ
ትዕዛዝ በሰጠበት
ደብዳቤ በኤምባሲው
ፈቃድ መክኖ
የነበረው የኤምባሲው
ካርታ ተመልሶ
ሥራ ላይ
እንዲውል የቀድሞው
ትዕዛዝ እንዲሻር፣
ለአትሌቶቹ ተመሳሳይ
ቦታ እንዲዘጋጅ፣
ይህ ሁሉ
ተከናውኖ በሁለት
ሳምንት ጊዜ
ውስጥ ሪፖርት
እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ
አስተዳደር ዋና
ሥራ አስኪያጅ
ትዕዛዝ የደረሰው
የአስተዳደሩ የመሬት
ልማት አስተዳደር
በተዋረድ ለቦሌ
ክፍለ ከተማ
ትዕዛዝ መስጠቱን
ተከትሎ አትሌቶቹ
የተሰማቸውን ቅሬታ
ለተለያዩ የአስተዳደሩ
አካላት እየገለፁ
መሆናቸው ታውቋል፡፡
በ1997 ዓ.ም. አስተዳደሩ
አትሌቶችን በመሰብሰብ
"". እናንተ ለአገር
ጥሩ ሰርታችኋል፡፡
በላባችሁ ባገኛችሁት
ገንዘብ መሬት
ቢሰጣችሁ በሊዝ
ገዝታችሁ ከባንክ
ሳትበደሩ ማልማት
ትችላላችሁ" በማለት
መሬት በሊዝ
እንዲወስዱ መጠየቃቸውን፣
እነሱም እጣ
በማውጣት በአስተዳደሩ
ጥያቄ መሠረት
የሊዝ ክፍያውን
አጠናቀው ሃያ
ሁለት ማዞሪያ
ትራፊክ ጽ/ቤት
የያዘው መሬት
ቢሰጣቸውም የትራፊክ
ጽሕፈት ቤቱ
ቦታውን እፈልገዋለሁ
በማለት ለዓመታት
ክርክር ሲካሄድ
ቆየ፡፡ አትሌቶቹ
ከአራት ዓመት
በኋላ በቦሌ
አካባቢ ተለዋጭ
ቦታ እንደተሰጣቸው
ለዲዛይን፣ ለአፈር
ምርመራና በዲዛይኑ
መሠረት ለሕንፃ
ግንባታ የሚሆን
እቃ ከውጪ
አገር በውጪ
ምንዛሬ ማዘዛቸውን
ይናገራሉ፡፡
"ኤምባሲው ቀደም
ሲል ለደህንነቴ
ያሰጋኛል፡፡ ለሌሎች
አልሚዎች ይሰጥ
ያለውን ቦታ
መልሶ ይሰጠኝ
ሲል ፈቃድ
መስጠት የልጆች
ጨዋታ ይመስላል"
በማለት ቅሬታቸውን
ያቀረቡት የአትሌቶቹ
ቤተሰቦች "አንድ
ጊዜ ውሰድ፣
አንድ ጊዜ
መልስ ማለት
አሳዛኝ ነው"
ብለዋል፡፡ ቦታውን
ከተነጠቁት አትሌቶች
መካከል "መንግሥት
እንደ ዜጋ
እያየን አይደለም
እየተጉላላን ነው"
በማለት ቅሬታዋን
ገልፃለች፡፡
70 ሚሊዮን ብር
የሚፈጅ ሕንፃ
ለማስገንባት ዝግጅታቸውን
ያጠናቀቁትን አትሌት
ጥሩነሽ ዲባባና
ባለቤቷ አትሌት
ስለሺ ስህን
ስለጉዳዩ ተጠይቀው
"ጉዳዩ ለሚመለከታቸው
የበላይ ባለሥልጣናት
አቤቱታቸውን በየደረጃ
እያቀረብን ነው"
ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ
አስተዳደርን በስልክ
ለማነጋገር ያደረግነው
ሙከራ አልተሳካም፡፡
የቦሌ ክፍለ
ከተማ ግን
"ትዕዛዝ ከተሰጠ
ተግባራዊ ማድረግ
ግዴታችን ነው"
የሚል መልስ
ሰጥቷል፡፡
በተያያዘ ዜና
በተመሳሳይ መልኩ
ሚሌኒየም አዳራሽ
ጐን ለአትሌት
ኃይሌ ገ/ስላሴ
የተሰጠው መሬት
ውዝግብ ተነስቶበት
ወደ ልማት
ሳይገባ እንደቆየ
ለማወቅ ተችሏል፡፡
|